About

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ይከበር!

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው እንደልጅ ተወልደው ጡቷን ጠብተው፣ ዳቤዋን በልተው፣ ከክብር ቦታ ደርሰው ሥርዓቷን ወደጎን ብለው፣ይልቁንም በሃይማኖት ከማይመስሉን ጋር በማበር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለውርደት፣ ልጆቿን ለስደት የዳረጉትን የቤተ ክርስቲያን አባት መሰሎችን፣ ነገር ግን አሳዳጆችን፥ ልጅ መስለው ነገር ግን በውስጧ ምንፍቅና የሚዘሩን፥ በአጠቃላይ ለሥርዓቷ የማይገዙትን ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ እታች እስካሉት ለሥርዓቷ ግድ የሌላቸውን፣ ይልቁንም የግል ሃብታቸውን እና እውቅናቸውን ለማትረፍ ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና የሚሉትን እኛን መስለው ሊነጥቁን የተነሱብንን አጥብቄ እቃወማቸዋለሁ፣ ለሥርዓቷም መከበር የበኩሌን አደርጋለሁ፣ እወነቱን በመመስከር፣ ቤተ ከርስቲያንን ከሚያውኩት ጋር ባለመተባበር፣ ለሥርዓቷ የማይገዙትን በመቃወም፣ ተው በማለት እረዳለሁ። ለዚህም የቅዱሳን አምላክ ይርዳን አሜን